ተፍጥሮአዊ ወሊድ መቆጣጠርያ
ተፍጥሮአዊ ወሊድ መቆጣጠርያ
- የወር አበባ
- ነቀላ ና የመሳሰሉት
በዛሬው ፖስታችን እንዴት የወር አበባን ለወሊድ መቆጣጠርያነት መጠቀም አንደሚቻል እናያለን:: ወደ ሳይንሱ በጥልቁ ሳንገባ በፊት በቀላል አባባል የወር አበባን ለወሊድ መቆጣጠሪያ ስንል ምንማለታችን ነው ? በአማካይ የወር አበባ ዑደት(cycle) 28-29 ቀናት የፈጃል: ቢሆንም እንቁላል ለመፈጠር 14 ቀናት በአማካይ ይወስዳል። ግን አንቁላል ከተፍጠረ ቦሀላ 3-5 ቀናት ብቻ ነው በሕይወት ሊቆይ የሚቺለው : በተመሳሳይ ሁኔታ ስፐርምም በሕይወት የሚቆየው 5-6 ቀናት ነው : ከነዚህ ቀናት ውጪ የግብረ ስጋ ግንኝነት : ብናደርግ የማርገዛችን ዕድል ጠባብ ነው ::
የወር አበባን ዑደት በመጠቀም እርግዝናን በ70ፐርሰንት መቀነስ ይቻላል:: ቀጥሎ ደግሞ እንዴት እንደምንጠቀም እናያለን:
ቀጥታ ወደ አተገባባሩ ሳንገባ በፊት :
ማስጠንቀቂያ :
- ቢያንስ ለስድስት ወራት የወር አባባችን ፀባይ መከታተል አለብን በተለይ ይህንን የወሊድ መከላከያ ዘዴ ውጤታማ ለማረግ ረጅሙን እና አጭሩን የወር አበባ ጊዜ መለየት ይገባል።
- እርግዝናን በ70ፐርሰንት ብቻ ነው መቀነስ የሚቻለው ቢያንስ በዚህ ዘዴ::
- በዚህ ፖስት ላይ የተጠቀሰው ምሳሌ ብቻ ነው : የእያንዳንዱ ሰው የወር አበባ ዑደት ይለያያል ።
- የወር አበባ ዑደት ከ27 ቀናት በታች ከሆነ ይሄ ዘዴ አይሰራም
አስፈልጊ ቁሶች :
- ጊዜውን የጠበቀ ቀን መቁጠሪያ ወይም ካላንደር
- እስክርብቶ
አጠቃቀም :
ለስድስት ወራት የወር አበባችን ዑደት ምንያህል ቀናትን አንደ ወሰደ አንመዘግባለን :
ለምሳሌ በተከታታይ ለስድስት ወራት የሚከተሉትን ቀናት ወሰደ እንበል ( 26 ፣29፣30፣29፣29፣29)
ዝቅተኛው 26 ከፍተኛው 30 ቀናት ናቸው ይህንን የወሊድ መከላከያ ዘዴ ውጤታማ ለማረግ ዝቅተኛውን እና ከፍተኛውን የዑደት ጊዜ አንይዛለን::
ሌላው ወሳኝ ነገር የመጣበትን ቀን መቁጠር ነው ::መቁጠር : የምንጀምረው: ፔሬድ :የታየበትን ቀን :አይደለም :በደንብ :የፈሰሰበትን :ቀንን አንድ :አንላለን :ቀን :መቁጠርያችን ላይ :ምልክት አናረጋለን: ከዚያ :ተመልሶ :የመጣበትን :ቀን ላይ ምልክት አናረጋለን : ከዚያ በሁላቱ ቀናት መካከል ያሉትን ቀናት አንቆጥርና: ውጤቱም የዑዳታችን (cycle)ርዝመት ነው ማለት ነው ::
- እንበልና የወር አበባ የመጣው በግንቦት (2)(ወይንም በደንብ የፈሰሰበት ) ግንቦት 2 ነው እንበል ይሄኑኑ በቀንመቁጠርያችን ምልክት እናረጋለን።
- አጭሩን የመዘገብነውን የዑደት ርዝመት ላይ 18 እንቀንስና ከመጀመሪያው ቀን ጀምረን ቆጥረ ን :ምልክት እናረጋለን። በዚህ ምሳሌ ላይ አጭሩ ቀን 26 ነው :ስለዚህ መልሳችን 8 ይሆናል ማለት ነው ። በነዚህ ቀናት እርግዝና አይፈጠርም: ካላደሩ ላይ በአረንጉአዴ ቀለም ተመልክቷል።
- ቀጥሎ ረጅሙን የመዘገብነውን የዑደት ቀን ላይ 11 እንቀንሳለን :እዚህ ምሳሌ ላይ 30 ስለሆነ 19 እና ገኛለን ። ይሄንኑ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቆጥረን ምልክት እናረጋለን። ከዚህ ቀን ቀጥሎ ያሉት ቀናት እስከ ድጋሚ መምጫው ቀን ባሉት ቀናት እርግዝና አይፈጠርም። ግን በመሃል ያሉት ቀናት ለእርግዝና አመቺናቸው ::
- መምጫው ቀን በቀስት ተመልክቷል።
ካላንደራችን የሚከተለውን ይመስላል ማለት ነው ።ጥያቄ ካላችሁ ከታች (comment ) ያርጉ ።